The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe moon [Al-Qamar] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah The moon [Al-Qamar] Ayah 55 Location Maccah Number 54
የትንሳኤ ቀን ተቃረበ:: ጨረቃም ተገመሰ::
ከሓዲያን ተዐምርን ቢያዩም እንቢ ብለው ይዞራሉ:: «ይህ ዘውታሪ ድግምት ነው» ይላሉ::
አስተባበሉም :: ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ:: ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው) ረጊ ነው።
ከዜናዎቹ በእርሱ ውስጥ መገሰጫ የሚሆን ነገር ያለበት በእርግጥ መጣላቸው::
ሙሉ ከሆነ ጥበብ (መጣላቸው):: ግን አስፈራሪዎች (ለማያምኑት) አይፈይዱም።
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ተውና ዙር። (ይልቁንስ) ጠሪው መልዓክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ።
ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነውና ፍጹም የተበተኑ አንበጣ መስለው ከየመቃብሮቻቸው ይወጣሉ::
ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎችና ቸኳዩች ሆነው ይወጣሉ:: ከሓዲያን ያን ጊዜ «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ።
ከእነርሱ በፊት የ(ነብዩ) ኑህ ህዝቦች አስተባበሉ:: ባሪያችንንም ኑህን አስተባበሉ:: «ዕብድ ነዉም» አሉት:: ተገላመጠም::
«ጌታውንም እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ተጣራ::
ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን::
የምድርንም ምንጮች በሃይል አፈነዳን:: የሰማዩና የምድሩ ውሃዉም ቀድሞ በተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ::
ባለ ብዙ ሳንቃዎችና ባለ ብዙ ሚስማሮች በሆነቸው ታንኳ ላይም ጫንነው::
በጥበቃችን ስር ሆና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረ ሰው ምንዳ ይህን ሰራን።
ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት:: ተገሳጭ አለን?
ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?
ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገንዛቢ አለን?
የዓድ ህዝቦች አስተባበሉ:: ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ፤
እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በሆነ ቀን በኃይል የምንትሻሻ ነፋስን ላክንባቸው::
ሰዎችንም ልክ ከስሮቻቸው እንደተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከየተደበቁበት ትነቅላቸዋለች::
ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?
ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?
የሰሙድ ህዝቦች በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::
(እንዲህም) አሉ: «ከእኛ የሆነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያ! ጊዜ በስህተትና በእብደት ውስጥ ነን አሉ።
«ከእኛ መካከል በእርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራዕይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» አሉ::
ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ::
እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን:: ተጠባበቃቸዉም ታገስም::
ውሃዉም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው:: ከውሃ የሆነ ፈንታ ሁሉ በየተራ የሚጣዱት ነው።
ጓደኛቸውንም ጠሩት:: ወዲያዉም (ሰይፉን) ተቀበለ:: ወጋትም::
ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?
እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው። ወዲያዉም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ እርጋፊ ሆኑ።
ቁርኣንን ለመገንዘብ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?
የ(ነብዩ) ሉጥ ህዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::
እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስ ላክን:: የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው::
ከእኛ በሆነ ጸጋ አዳናቸው:: ልክ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን::
ብርቱ አያያዛችንን በእርግጥ አስጠነቀቅናቸው:: በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ።
ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት። ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን። ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎቹን ቅመሱ አልናቸው።
በማለዳም ዘወታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው::
ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎችም ቅመሱ ተባሉ::
40 ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?
የፈርዖንን ቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጧቸው።
በተዓምራታችንም በሁሏም አስተባበሉ:: የብርቱ ቻይንም አቀጣጥ ቀጣናቸው::
የእናንተ ከሓዲያኖቻችሁ ከእነዚያችሁ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለእናንተ በመጽሐፎች ውስጥ በተለየ የተነገረ ነፃነት አላችሁ?
ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉ?
ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ:: ጀርባዎቻቸውንም ያዞራሉ::
ይልቁንም ሰዓቲቱ ትንሳኤ ቀጠሯቸው ናት:: ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት::
አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው::
በእሳት ውስጥ በፊታቸው በሚጎተቱበት ቀን የሰቀርን (የገሀነምን) ቅጣት መንካትን ቅመሱ ይባላሉ::
እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው::
ትዕዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት የሆነች አንዲት ቃል እንጂ ሌላ አይደለችም::
ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፤ ተገሳጭ አለን?
የሰሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው::
ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተፃፈ ነው::
አላህን ፈሪ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው::
እነርሱም (ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ላይ ከሆነው ንጉስ አላህ ዘንድ ናቸው::

