The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesMutual Disillusion [At-Taghabun] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah Mutual Disillusion [At-Taghabun] Ayah 18 Location Madanah Number 64
በሰማያት ውስጥም ሆነ በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ አላህን ያሞግሳል:: ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ምስጋናም ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::
እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው:: ከእናንተም መካከል ከሓዲ አለ:: ከእናተም መካከል አማኝ አለ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::
(እርሱ) ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም አሳመረ፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው::
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: የምትደብቋትንም ሆነ የምትገልጡትን ያውቃል:: አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
የእነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክህደታቸውን ቅጣት የቀመሱ ህዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
ይህ (ቅጣት) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው አስረጂዎችን ይዘው ሲመጡላቸው «ሰዎች ይመሩናልን?» ስላሉና ስለ ካዱ፤ ከእምነትም ስለ ዞሩ ነው:: አላህ ከእነርሱ እምነት ተብቃቃ:: አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በፍጹም የማይቀሰቀሱ መሆናቸውን አሰቡ። «(እንዴት አትቀሰቀሱም?) በጌታየ ይሁንብኝ ትቀሰቀሳላችሁ:: ከዚያ ትፈጽሙት የነበረውን ተግባራችሁን ትናገራላችሁ:: ይህ ተግባር ለአላህ ቀላል ነው» በላቸው።
በአላህ በመልዕክተኛውና በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑም:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና።
(ይኸዉም) ለመሰብሰቢያው ቀን የሚሰበስባችሁ እለት አስታውሱ:: ይህ ቀን የቁጭት ቀን ነው:: በአላህም የሚያምን ሰው መልካምንም የሚሠራ ከርሱ ኃጢአቶቹን ይሰርይለታል፤ (ይፍቅለታል)፤ ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባት ገነቶች ለዘላለም ያስገባዋል:: ይህ ታላቅ እደለኝነት ነው::
እነዚያም የካዱትና በአንቀፆቻችንም ያስተባበሉት የዝንታለም እሳት ባለቤቶች ማለት እነርሱ ናቸው:: (ጀሀነም) መመለሻነቷ ምን ይከፋ!
ከመከራም በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ማንንም አይነካም:: በአላህ የሚያምን ሰው አላህ ልቡን ለትግስት ይመራዋል:: አላህም በሁሉም ነገር አዋቂ ነው::
አላህን ታዘዙ መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ብትዞሩም (መልዕክተኛውን አትጎዱም::) በመልዕክተኛችንም ላይ ያለበት በግልጽ ማድረስ ብቻ ነው::
አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ::
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለእናንተ ጠላቶች የሆኑ አሉ:: ስለዚህ ተጠንቀቋቸው:: ይቅርታ ብታደርጉ፤ ብታልፏቸዉም፤ ብትምሩዋቸዉም፤ አላህ በጣም መሀሪ፤ አዛኝ ነው::
ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው:: አላህም ከእርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለ::
አላህንም የቻላችሁትን ያህል ፍሩት:: ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ይሰጣችኋልና:: የነፍሶቻቸዉን ንፍገት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው::
ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩት (ምንዳውን) ለእናንተ ይደራርበዋል:: ለእናንተም ይምራል:: አላህ አመስጋኝና ታጋሽ ነውና::
(እርሱ) ስውሩንም ይፋዉንም ሁሉን አዋቂ ኃያልና ጥበበኛ ነዉና።

