The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe reality [Al-Haaqqa] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah The reality [Al-Haaqqa] Ayah 52 Location Maccah Number 69
እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሳኤ)::
አረጋጋጪቱ (እርሷ) ምንድን ናት!
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አረጋግጪቱም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
የሰሙድና የዓድ ህዝቦች በቆርቋሪይቱ (ትንሳኤ) ቀን አስተባበሉ::
የሰሙድ ህዝቦችማ ወሰን በሌላት ነፋስ ጩኸት ተጠፉ::
የዓድ ህዝቦችማ በኃይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ::
ተከታታይ በሆነ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት ቀናቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት:: ህዝቦችንም፤ በውስጧ የተጣሉ ሆነው ልክ ክፍት እደሆኑ የበሰበሱ የዘንባባ ግንዶች ታያቸዋለህ::
ከእነርሱ መካከል ቀሪን ታያለህን?
ፈርዖን፤ ከበፊቱ የነበሩትን ሰዎችም፤ ተገልባጮችም (የሉጥ ሰዎች ከተሞች) ኃጢአት ፈጸሙ።
የጌታቸውንም መልዕክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፤ የበረታችንም ቅጣት ቀጣቸው::
እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሳፋፊይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ::
ይህንም ያደረግነው ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋትና አጥኚ የሆነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ ነው::
በቀንዱ አንዲት መነፋት በተነፋች ጊዜ::
ምድርና ጋራዎች (ከየስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፤
በዚያ ቀን (ትንሳኤ) ትከሰታለች::
ሰማይም ትቀደዳለች:: በመሆኑም እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፤
መላዕክትም በየጫፎቿ ላይ ይሆናሉ:: የጌታህንም ዓርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላዕክት ከበላያቸው ይሸከማሉ::
በዚያ ቀን ከናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲሆኑ ትቀረባላችሁ::
ያ መጽሀፉን በቀኝ እጁ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ እንዲህ) ይላል: «እንኩ መጽሐፌን አንብቡ፤
«እኔ ምርመራየን የምገናኝ መሆኔን አረጋገጥኩ።» (ይላል)
እርሱም በተወደደች ኑሮ ውስጥ ይሆናል::
በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፤
ፍሬዎቿ ቅርቦች የሆኑ::
በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም ይባላሉ::
ያ መጽሐፉን በግራው የተሰጠ ሰው ደግሞ (እንዲህ) ይላል: «ዋ ጥፋቴ ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ፤
«ምርመራዬም ምን እንደሆነ ባላወቅሁ፤
«ሞት ምነው የህይወቴ የመጨረሻ ፍፃሜ በሆነች፤
«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አልጠቀመኝም፤
«ስልጣኔ ከእኔ ላይ ጠፋ» ይላል::
ያዙት ከዚያ እጁን ከአንገቱ ጋር እሰሩት፤
ከዚያ በእሳት ውስጥ አስገቡት፤
ከዚም እርዝመቷ ሰባ ክንድ በሆነች ሰንሰለት ውስጥ አስገቡት።
እርሱ ታላቅ በሆነው አላህ አያምንም ነበርና፤
ድሆችንም በማብላት ላይ አያነሳሳም ነበርና::
ለእርሱ ዛሬ እዚህ ቦታ ዘመድ ማንም የለዉም::
ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ እዥ በስተቀር የለዉም::
ይህን ምግብ ኃጢአተኞች እንጂ ሌላ አይበላዉም ይባላል::
በምታዩት ነገር ሁሉ እምላለሁ ::
በማታዩትም ነገር ሁሉ እምላለሁ ::
ቁርኣን የተከበረው መልዕክተኛ ቃል ነው።
እርሱም የባለ ቅኔ ገጣሚ ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ::
የጠንቋይም ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ::
ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::
በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት እንኳን (ያላልነው) በቀጠፈ ኖሮ፤
በኃይል በቀጣነው ነበር::
ከዚያ ከእርሱ የልቡን ስር የተንጠላጠለበትን (ጅማት) በቆረጥን ነበር::
ከናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም።
እርሱ (ቁርኣን) ለጥንቅቆቹ ብቻ መገሰጫ ነው::
እኛም ከናንተ ውስጥ አስተባባዩች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን::
እርሱ (ቁርኣንም) በከሓዲያን ላይ ጸጸት ነው::
እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው::
እናም የታላቁን ጌታህን ስም (ታላቁን ጌታህን) አጥራው::

