The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Jinn [Al-Jinn] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Jinn [Al-Jinn] Ayah 28 Location Maccah Number 72
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን አዳመጠው እንዲህ ማለታቸው ተወረደልኝ በል: «እኛ አስደናቂ የሆነን ቁርአን ሰማን፤
2. «ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርኣን ሰማን) በእርሱም አመንን:: በጌታችን አንድንም አናጋራም::
3. «እነሆ የጌታችን ክብር ላቀ:: ሚስትንም ልጅንም አልያዘም::
4. «እነሆ ቂላችን በአላህ ላይ ወሰን ያለፈን ውሸት ይናገር ነበር::
5. «እኛም ሰዎችና ጋኔኖች በአላህ ላይ ውሸትን ቃል አይናገሩም ማለትን ጠረጠርን» አሉ በማለት ወደእኔ ተወረደ በል።
وَأَنَّهُۥ كَانَ رِجَالٞ مِّنَ ٱلۡإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٖ مِّنَ ٱلۡجِنِّ فَزَادُوهُمۡ رَهَقٗا [٦]
6. እነሆ ከሰዎች የሆኑ ወንዶች ከአጋንንት በሆኑ ወንዶች ይጠበቁ ነበር። ኩራትንም (ጥመትን) ጨመሯቸው።
7. አላህ አንድንም አይቀሰቅስም ማለትን እንደጠረጠራችሁ እነርሱም ጠረጠሩ::
8. እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት::
9. እኛም ከእርሷ ወሬን ለማዳመጥ በመቀመጫዎች እንቀመጥ ነበር:: አሁን (ግን) የሚያዳምጥ (ሁሉ) ተጠባባቂ የእሳት ችቦ ያገኘዋል።
وَأَنَّا لَا نَدۡرِيٓ أَشَرٌّ أُرِيدَ بِمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ أَرَادَ بِهِمۡ رَبُّهُمۡ رَشَدٗا [١٠]
10. እኛም በምድር ውስጥ ባሉት ክፉ ተሽቷል? ወይስ በእነርሱ (በኩል) ጌታቸው ደግን ነገር ሽቷል? ማለትን አናውቅም።
11. ከእኛም ውስጥ ደጋጎች አሉ:: ከእኛም ውስጥ ከዚህ ሌላ የሆኑ አሉ:: የተለያዩ መንገዶች ባለቤቶች ነበርን::
12. እኛም አላህን በምድር ውስጥ ፈጽሞ የማናቅተው ሸሽተንም ፈጽሞ የማናመልጠው መሆናችንን አረጋገጥን::
13. እኛም መሪውን በሰማን ጊዜ በእርሱ አመንን:: ያ! በጌታው የሚያምን ሰው ሁሉ መጎደልንም ሆነ መጨመርን አይፈራም::
14. ከእኛም ውስጥ ሙስሊሞች አሉ:: ከእኛም ውስጥ በዳዩች አሉ:: እነዚያ የሰለሙ ሰዎች ቅንን መንገድ መረጡ::
15. እነዚያ በዳዩችማ ለገሀነም ማገዶ ሆኑ::
16. (ሰዎች ሁሉ በአላህ) በመንገድ ላይ ቀጥ ባሉ ኖሮ ብዙ ዝናብን ባጠጣናቸው ነበር::
17. በእርሱ ልንፈትናቸው (ባጠጣናቸው ነበር)። ያ ጌታውን ከማስታወስ የሚያፈገፍግ ሰው አስቸጋሪ ቅጣት ውስጥ ያስገባዋል::
18. መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው:: እናም በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ማለትን ተወረደልኝ::
19. እነሆ የአላህ ባሪያ (ሙሐመድ) አላህን የሚጠራው ሆኖ በተነሳ ጊዜ ጋኒኖቹ በእርሱ ላይ ድርብርቦች ሊሆኑ ቀረቡ::
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ የማመልከው ጌታየን ብቻ ነው:: በእርሱ አንድንም አላጋራም» በል።
21. «እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ሆነ ማቅናትን አልችልም» በል።
22. «እኔን ከአላህ ቅጣት አንድም (አካል) አያድነኝም:: ከእርሱ ሌላ መጠጊያም አላገኝም» በል።
23. ከአላህ የሆኑ መልዕክቶችን ከማድረስ በስተቀር አልችልም:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚያምጽ ሁሉ ለእርሱ የገሀነም እሳት አለው:: በውስጧም ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ።
حَتَّىٰٓ إِذَا رَأَوۡاْ مَا يُوعَدُونَ فَسَيَعۡلَمُونَ مَنۡ أَضۡعَفُ نَاصِرٗا وَأَقَلُّ عَدَدٗا [٢٤]
24. የሚስፈራሩበትንም ባዩ ጊዜ ረዳተ ደካማ ቁጥሩም አነስተኛ የሆነው ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ::
25. «ያ! የምትስፈራሩበት ነገር ቅርብ ወይም ጌታየ ለእርሱ የተወሰነ ጊዜን የሚያደርግለት እሩቅ መሆኑን አላውቅም።» በላቸው
26. እርሱም እሩቁን ሚስጢር አዋቂ ነው::በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»
27. (በሚስጢሩም ላይ) ከመልዕክተኛው ለወደደው ቢሆን እንጂ (ለሌላ አንድንም አያሳውቅም):: አይገልጽም:: ለእርሱም ከበስተፊቱም ከበስተኋላዉም ጠባቂዎቸን ያደርግለታል::
28. ከእነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀት የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲሆን የጌታቸውን መልዕክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ (ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል)::