The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Most High [Al-Ala] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Most High [Al-Ala] Ayah 19 Location Maccah Number 87
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታህን ስም አጥራ (አሞግስ)።
2. ያ ሁሉን ነገር የፈጠረውንና ያስተካከለውን፤
3. ያን የወሰነውን ነገርንም ሁሉ ለተፈጠረለት የመራውን፤
4. ያም ግጦሽን ለምለም አርጎ ያወጣውን፤
5.(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፤
7. አላህ ከፈለገው ነገር በስተቀር፤ እናም እርሱ ግልጹንም የሚሸሽገውንም ሁሉ ያውቃልና፤
8. ለገሪቱም (ሕይወት እስላምን ትከተል ዘንድ) እናገራሃለን።
9. (ሰዎችንም) ገስፅ፤ ግሳፄይቱ ብትጠቅም።
10. (አላህን) የሚፈራ በእርግጥ ይገሰፃል።
11. መናጢዉም ይርቃታል::
12. ያ! ታላቂቱን እሳት የሚገባው፤
13. ከዚያም በእርሷ ውስጥ የማይሞትና ህያዉም የማይሆነው።
14. (አላህን ከማመፅ) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፤
15. የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ::
16. ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ታስቀድማላችሁ፤
17. (ሰዎች ሆይ!) መጨረሻይቱ ሕይወት በላጭና፤ ዘወታሪ ሆና ሳለ።
18. ይህ በቀደምቶቹም መጻሕፍት ውስጥ ያለ ነው።
19. በኢብራሂምና በሙሳ መጽሐፍት ውስጥ የሰፈረ እውነታ ነው።