The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesSolace [Al-Inshirah] - Amharic translation - Africa Academy
Surah Solace [Al-Inshirah] Ayah 8 Location Maccah Number 94
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልብህን ላንተ አላሰፋንልህም?
2. ሸክምህንም አወረድንልህ?
3. ያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)
4. መወሳትህንም ከፍ አላደረግንልህ?
5. እናም ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ::
6. ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ::
7. (የጀመርከውን ጥሩ ስራ) በጨረስክ ጊዜ ወደ ሌላ ጥሩ ስራ ቀጥል (አስከትል)።
8. ክጃሎትህንም ወደ ጌታህ ብቻ አድርግ።