The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Fig [At-Tin] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah The Fig [At-Tin] Ayah 8 Location Maccah Number 95
በበለስና፤ በወይራ ዛፍ እምላለሁ፣
በሲና ተራራም፤
በዚህ በጸጥተኛው (ጸጥታ በነገሰበት) አገር መካም እምላለሁ።
በርግጥ ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው::
ከዚያም (ከፊሉን) ከበታቾች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው::
እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባራት የሰሩት ሲቀሩ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አለላቸው::
(የሰው ልጅ ሆይ) ታዲያ ከዚህ (እውነታ) በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?
አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን?

