The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Power [Al-Qadr] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Power [Al-Qadr] Ayah 5 Location Maccah Number 97
1. እኛ (ቁርኣንን) በመወሰኛይቱ ሌሊት ውስጥ አወረድነው።
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመወሰኛይቱ ሌሊት ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
3. የመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር የምትበልጥ ነች።
4. በእርሷ ውስጥ መላዕክትና ሩሕም (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በሁሉም ጉዳዮች ይዘው ይወርዳሉ።
5. እርሷም ጎህ እስኪወጣ ድረስ ሰላም ነች።